ሸገር የህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ማህበር ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መጽሐፍትን ለወረዳው አስተዳደር ማስረከቡን ገለጸ፡፡
ግንቦት 15፣ 2014

ሸገር የህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ማህበር ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት አገልግሎት የሚውል በግምት ከ45 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ 297 መጽሐፍትን ለወረዳው አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ፣ ለሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊና ለወጣት ሊግ ሰብሳቢ ማስረከቡን ገልጿል፡፡
ለወረዳው አስተዳደር 50 አይነት የመማሪያ መጽሐፍትን፣ የሳይንስ አጋዥ መጽሐፍትን እና የልብወለድ መጽሐፍትን ከድርጅቱ ሰራተኞች በማሰባሰብ ለወረዳው አስተዳደር ማስረከባቸውን የገለጹት የሸገር ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ማህበር ዋና ዳሬክተር አቶ ሲሳይ አለማየሁ አላማውም የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህጻናትን በእውቀት የበለጸጉ እና ምክንያታዊ ሆነው እንዲያድጉ ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ ድርጀቱ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ታስቦ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አቶ ሲሳይ አክለውም ድርጅቱ በቀጣይ ህጻናት ሁለንተናዊ ስብዕናቸው በተሟላ ሁኔታ እንዲመቻችላቸው በሚደረገው ስራ ሁሉ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የወረዳው አፈገ-ባኤ የሆኑት አቶ በሃይሉ እምወድ ድርጅቱ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለሚፈራበት ቤተ መጻህፍት አገልግሎት የሚውል መጽሐፍትን ሰራተኞችን በማስተባበር ድጋፍ በማድረጋቸው ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

የወረዳው አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ መጽሀፍቱን ሲረከቡ
መጽሀፍቱ በከፊል

ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ መጽሀፍቱን ሲረከቡ